Quantcast
Channel: College of Human Sciences
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2018

Guides to enhance strategies for prevention of mother-to-child transmission (PMTCT) of HIV in the North-East Ethiopia

$
0
0
Guides to enhance strategies for prevention of mother-to-child transmission (PMTCT) of HIV in the North-East Ethiopia Yimer, Hawa Wolie ከእናት ወደ ልጅ እችአይቪ የሚተላለፍበትን መንገዶችን ለመቀነስ የ “PMTCT” አገልግሎት ጥራትን መጠበቅ እና የነፍሰ ጡር እናቶች የPMTCT ፕሮግራም አገልግሎት ተጠቃሚ ሁኔታን ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ አላማከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ነፍሰጡር እናቶች ተመክሮን እንዲሁም ከእናቶች ወደ ህፃናት የቫይረስመተላለፍ ሁኔታን ለመከላከል በሚከናወነው ፕሮግራም (PMTCT) ላይ ተሳተፊ የሆኑ ነርሶች እና አዋላጆችን እይታለመገንዘብእንዲሁምየPMTCTየመከላከያፕሮግራምስልቶችንለማሳደግየሚያስችሉመሪሪያዎችንለማዘጋጀትነው፡፡ጥናታዊ ጽሁፍ በተጨማሪም ኤችአይቪ ከእናቶች ወደ ህፃናት የሚተላለፍበትን አጋጣሚ ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ፣ከኤችአይቪ ነፃ የሆነ ትውልድን ለማዘጋጀት ያቀደ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የተካተተው የኬዝ ጥናት ንድፍ የተከናወነውከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ነፍሰጡር እናቶች ተሞክሮን ለመረዳት እንዲሁም የጤና አገልግሎት አቅራቢዎች (ነርሶች እናአዋላጆች) በPMTCT ፕሮግራም ላይ ያላቸውን ተሞክሮ እና ግንዛቤ ለመረዳት ነው፡፡የመረጃ ማሰባሰብ ሂደቱ ከፊል መዋቅር ያላቸው መጠይቆችን እንዲሁም ጥልቅ ቃለመጠየቆችን በማከናወን ተፈጽሟል፡፡ሁለትመልስ ሰጪቡድኖች በዚህ ጥናት ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ነፍሰጡር እናቶች እንዲሁም የPMTCT ፕሮግራም የጤና አገልግሎት አቅራቢዎች (ነርሶች እና አዋላጆች) ፡፡ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ነፍሰጡር እናቶችን የያዘውቡድን 16 አባላት የነበሩት ሲሆን እነዚህ አባላት በአሁኑ ጊዜ የPMTCT አገልግሎት እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛው ቡድንከጤና አገልግሎት አቅራቢዎች (ነርሶች እና አዋላጆች) የተውጣጣ ሲሆን 10 አባላት ነበሩት፡፡ እነዚህም አባላት በቅድመወሊድ ክሊኒኩ ውስጥ የPMTCT አገልግሎትን ያቀርቡ ነበር፡፡መረጃው ማጥራት በማከናወን፣ መረጃ በመመልከት እንዲሁም የጤና እሳቤ ሞዴልን በመጠቀም መደቦችን በማዘጋጀት ጽንሰ ሀሳባዊ መዋቅር አማካኝነት ትንተና ተከናውኖበታል፡፡ ከዚህም ባሻገር መመሪያዎቹን ለመደገፍ የተመጡት መንገዶችበምርመራ ግኝቶች እንዲሁም በተጨማሪ ጽሁፎች ግምገማ ላይ የተመረኮዙ ነበሩ፡፡ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች ያዘጋጅዋቸውዳሰሳዎችም በጉዳዩ ላይ ስምምነት ለመገንባት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ጥናቱ የእናቶችን እውቀት እና ግንዛቤ በአንክሮበማስተዋል የኤችአይቪ ከእናት ወደህፃናት የመተላለፍ ሁኔታ ላይ የጤና አገልግሎት አቅራቢዎችን አስተሳሰብ እናተሞክሮበPMTCT ላይ አጽንኦት ሰጥቶበታል፡፡እናቶች የPMTCTፕሮግራምላይ ያላቸውንተጠቃሚነት በተመለከተየጤና አገልግሎት አቅራቢዎችንተሞክሮ እናግንዛቤበተመለከተ ጠንካራ መረጃ በማሰባሰብ የእነርሱን ስጋት፣ በሽታው ሊሰራጭ የሚችልበትን እድል እንዲሁም የሴቶቹ ምልከታመመሪያዎቹን በማዘጋጀት በግብአትነት አገልግለዋል፡፡ይህበደህንነትቁርጠኝነትሞዴልላይየታዩትንውጤቶችበሚያስገኝአግባብየእናቶችንየPMTCTአጠቃቀምየሚያሳድግነው፡፡ ኤችአይቪ ከእናት ወደ ህፃን የሚተላለፍበትን ሁኔታ (MTCT) በመረዳት እና በመከላከል ኤችአይቪ ያልተያዘ ህፃንንለማግኘት ጥሩ እድል ይፈጠራል፡፡ የወንድ አጋሮች ተሳትፎ አስፈላጊነት በአጽንኦት መመልከት እና በጤና አገልግሎትአቅራቢዎች እና እናቶች መካከል ያለውን መስተጋብር በPMTCT አገልግሎት ላይ ማስጠበቅ አስፈላጊ ነበር (በርህራሄ እናበእንክብካቤላይየተመረኮዘግንኙነትንማስጠበቅ)፡፡በስፍራውላይ የነበሩየቅርብ የጤናሥራአስኪያጆችመመሪያዎችንእንዲቀበሉ እና ለአፈፃፀሙ አመቺ የሆነ ምህዳርን እንዲያቀርቡ ተመክሯል፡፡ Includes summary in Amharic

Viewing all articles
Browse latest Browse all 2018

Trending Articles